Fana: At a Speed of Life!

ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ነው።

በህወሓት ጁንታ ቡድን ጉዳት ደርሶበት የነበረው ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ ይገኛል።

እንደ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ የመስመሩ ጥገና በፍጥነት እየተከናወነ ነው የሚገኘው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ-ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው ማለታቸው እና ይህ ተግባር ሦስት መልኮች እንዳሉት መግለጻቸው ይታወሳል።

“ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር። እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋል” ማለታቸውም የሚታወስ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.