Fana: At a Speed of Life!

ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ 418 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በአስር ወራት 418 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 በጀት ዓመት በአስር ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ 498 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቀዶ 418 ሚሊየን ዶላር ገቢ በማስመዝገብ የዕቅዱን 84 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ተገልጿል።

የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ102 ሚሊየን ዶላር ጭማሬ አሳይቷል ተብሏል።

ገቢው ወደ ውጭ ከተላከ 146 ሺህ 342 ቶን ምርት የተገኘ ሲሆን÷ የተላከው የምርት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ17 ሺህ 634 ቶን ጭማሬ ማስመዝገቡን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት 153 ሚሊየን ዶላር፣ ምግብና መጠጥ 93 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች 33 ሚሊየን ዶላር፣ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች 22 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር፣ ማምረቻው ዘርፍ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ 16 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር እና ሥጋና ወተት አፈፃፀም 98 ሚሊየን ዶላር ድርሻ አላቸው።

ከአጎዋ የገበያ እድል መቋረጥ ጋር ተያይዞ አምራቾች ያጡትን የገበያ እድል ሊተኩ የሚችሉ አማራጭ ገበያ መዳረሻዎችን ለመለየት ጥናት የማካሄድ ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.