Fana: At a Speed of Life!

ከአሰላ ከተማ የሀገር ጥሪ ተቀብለው የመከላከያ ሰራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሰላ ከተማ የሀገር ጥሪ በመቀበል ከስምንት ቀበሌዎች የተውጣጡ ወጣቶች የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
ወጣቶቹ ለሀገር ባላቸዉ ታላቅ ፍቅር እንዲሁም ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ለመከላከያ ሰራዊት ባላቸዉ ክብር ሰራዊቱን መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡
በስፍራዉ የተገኙ ወላጆችም የኛ የመኖር ህልውና በሀገር ሰላም መሆን ላይ የተመሰረተ ነዉና ልጆቻችንን ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት እንዲሰለፉ ሸኝተናል ብለዋል፡፡
የአሰላ ከተማ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሸምሰዲን መሀመድ በበኩላቸዉ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለመከላከል ዝግጁ የሆኑ ወጣቶችን የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን እንዲቀላቀሉ መልምለናል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ለሀገሩ ያለዉን ፍቅር ለመግለጽ እና ክብሯን ለማስጠበቅ ያሳየዉ ተነሳሽነትም የሚደንቅ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በልጆቻቸዉ ሲረዱ የነበሩ እና ልጆቻቸውን ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሰጡ ወላጆች ህብረተሰቡ አጋርነቱን እንዲያሳያቸዉም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሊያ ዱጉማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.