Fana: At a Speed of Life!

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የተላለፈ ማሳሰቢያ

በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንና በሰሜን ወሎ አካባቢዎች ለምትገኙ ሁሉ፤

ሀ/ ለሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ማጥቃት ጠላት ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሆኖበታል። የቻለውን ዘርፎ፣ ያልቻለውን አውድሞ ለመሸሽ ጠላት እየሞከረ ነው። አሸባሪው ኃይል በምንም መልኩ ከገባበት አካባቢ ተገቢውን ቅጣት ሳያገኝ መውጣት የለበትም። ወይ ይማረካል፤ ወይ ርምጃ ይወሰድበታል።

በመሆኑም፦

1. በተወረሩ አካባቢዎች የገባችሁ የአሸባሪው የህወሓት አባላት፣ የመከላከያ ኃይላችን በከፍተኛ ሁኔታ የህወሓትን ጦር እየደመሰሰ መሆኑን ዐውቃችሁ ሕይወታችሁን ለማትረፍ ስትሉ፣ በአስቸኳይ መሣሪያ አውርዳችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ እናሳስባለን፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ለሚደርስባችሁ ቅጣት ኃላፊነቱ የራሳችሁ ነው።

2. እጅ የሚሰጡ የአሸባሪው የህወሓት አባላትን ሕዝቡ በክብካቤ ይዞ ለጸጥታ አካላት እንዲያስረክብ፤ የጸጥታ አካላትም በሕግና በሥርዓት እንዲይዟቸው ትእዛዝ ተሰጥቷል።

ለ/ በተወረሩ አካባቢዎች ለምትገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች

1. በግንባርና በተወረሩ አካባቢዎች የምትገኙ መላው ሕዝባችን፣ ተደራጅታችሁ የዘረፈውን ንብረት በማስቀረት ፤ መኪናዎቹ እንዳያልፉ መንገዱን በሙሉ በድንጋይና በግንድ በመዝጋት የአሸባሪውን ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው፤ በየገደሉ፣ በየሸጡ፣ በየጫካው እየተደራጃችሁ ጠላት መግቢያ መውጫ እንዲያጣ በማድረግ፣ በምንም መልኩ ጠላት ወደኋላ እንዳይመለስ ባለበት እንድታስቀሩ ጥሪ ቀርቦላችኋል። አንድም ጠላት ወደ ኋላ ሸሽቶ ማምለጥ የለበትም። ወይ እጁን መስጠት አለበት ወይም ርምጃ ሊወሰድበት ይገባል።

2. ጠላት የጦር መሣሪያዎችን ይዞ ማምለጥ የለበትም። በየግንባሩ ያላችሁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጠላት ይዞ የሚሸሸውን ማንኛውም የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ጠላትን ማርካችሁ ወይም ደምስሳችሁ እንድትታጠቁ ፤ የቡድንና ሌሎች መሣሪያዎችን ደግሞ ማርካችሁ ለመከላከያ እንድታስረክቡ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ያሳስባል ፤ በምትኩ ሌላ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ይሰጣችኋል፤

ነጻነታችንን የምናውጀው በተባበረ ክንዳችን ነው፤

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.