Fana: At a Speed of Life!

ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ 400 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ እንደገለጸው፤በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በማይሰራ ላፕቶፕ ቦርሳ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቀጥጥር ሥር ውሏል።
ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ በላፕቶፕ ቦርሳ ለማሳለፍ የሞከረው አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በኤክስሬይ ፍተሻ አማካኝነት የተያዘ ሲሆን፤ በወንጀል ድርጊቱ ተባባሪ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሌሎች ሶስት ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።
በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉት አራት ተጠርጣሪዎችና አደንዛዥ እፁ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀረ አደገኛ ዕፅ ዲፓርትመንት መላካቸውም ተመልክቷል።
ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የፀጥታ አካላት በጋራ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በጥናት ላይ የተደገፈ የመረጃ ስራ እያከናወነ መሆኑን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.