Fana: At a Speed of Life!

ከአድዋ ድል የሃገሪቱ ፖለቲካና ፖለቲከኞች ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከታላቁ የአድዋ ድል የሃገሪቱ ፖለቲካና ፖለቲከኞች ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ ፖለቲከኞች ተናገሩ ፡፡

የትግራይ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እና የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ መጋቢ ብሉይ አብረሃም፥ ቀደምት አባቶችና እናቶች ስለ ሃገር አንድ ሆነው የከፈሉት መስዋእትነት ለታመመው ፖለቲካችን ማከሚያ እንደሚሆን አብራርተዋል ፡፡

ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ስለ ነጻነት በመተባበር ዘመናዊውን የጣልያን ጦር በወኔ መቀልበሳቸውን የሚያነሱት ፖለቲከኞቹ የነጻነት ቀንዲል ሆኖ ለትውልድ ከሚሻገረው ድል ፖለቲከኞች ቁም ነገሮችን ተግባር ላይ ማዋል ይገባናልም ብለዋል ፡፡

ከሚከፋፍሉ ሃሳቦች ይልቅ የሚያቀራርቡን እና አንድ የሚያደርጉን ጉዳዮች እንደመብዛታቸው ፖለቲከኞች ጠንካራ ሃገርን እውን በማድረግ ለሃገራዊ ራእይ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንዲሁም መጋቢ ብሉይ አብረሃም አስረድተዋል፡፡

የሁሉም ህዝቦች አሻራ ያረፈበት እና የጠንካራ ትብብር ተምሳሌት የሆነው የአድዋ ድል አሁንም ድረስ ላልተገራው ፖለቲካ መስመር ማስያዥያነት መጠቀም ይገባናል ሲሊም የፖለቲካ ፓርቲ የስራ ሃላፊዎቹ ተናግረዋል ፡፡

ቀደምት እናቶችና አባቶች በታላቅ ሃሳብ መስዋእት ሆነው ያስረከቧትን ሃገር ዛሬ ላይ በትናንሽ የሃሳብ ልዩነቶች ልናሳንሳት አይገባም ብለዋል ፖለቲከኞቹ ፡፡

በአወል አበራ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.