Fana: At a Speed of Life!

ከኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያን ዕድል የሚወስን ሌላ ምድራዊ ኃይል የለም – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ዕድል የሚወስነው የአገሩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ሌላ ምንም ምድራዊ ሃይል ሊኖር እንደማይችል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ አስገነዘቡ።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ በትህነግ ቡድን የእብሪት ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብዓዊ ደጋፍ ለማድርግ ኢትዮጵያውያን ባዘጋጁት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ የአገራቸውን መፃኢ ዕድልና ጉዞ ለመወሰን ህጋዊ ኃይልና ሉዓላዊ መብት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናቸውን አስምረውበታል።

አምባሳደር ታዬ ይህን የገለጹት፥ የኢትዮጵያ የሰላምና እንድነት ማህበር የተሰኘው ተቋም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀውና በአሸባሪው ህወሃት ወረራና ጥቃት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አምባሳደር ታዬ አክለውም፥ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አገራቸው የምትገኝበትን ሁኔታ በተሟላ ሁኔታ በመገንዝብና የላቀ ጥበብ በማሳየት አገራቸውን ከፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር በትጋት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በበኩላቸው፥ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ለተፈናቃይ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ይውል ዘንድ 500 ሺህ የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው፥ በቀጣይም የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.