Fana: At a Speed of Life!

ከእንጨት የተሰሩ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በቋሚነት በኮንክሪት የመቀየር ስራ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከእንጨት የተሰሩ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በቋሚነት በኮንክሪት የመቀየር ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች በአየር ጸባይ እና በሰው ሰራሽ ችግሮች ሳቢያ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ ይገለጻል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም በተለያዩ አካባቢዎች ባደረገው ቅኝት ችግሩ በስፋት መስተዋሉን ለመታዘብ ችሏል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ÷ ችግሩን ለማስወገድ ተቋሙ ከእንጨት የተሰሩ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በቋሚነት በኮንክሪት የመቀየር ስራ መጀመሩን ተናግረዋል፡
በዚህ መሰረትም አሁን ላይ ከእንጨት ወደ ኮንክሪት ምሶሶ የመቀየር እና የሃይል መቆራረጡን ስራ ለማስቀረት ከአዲስ አበባ እስከ 50 ኪሎ ሜትር ባሉ ከተሞች ላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ በ7 በተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች ሐዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ጅማ፣ መቀሌ ፣ድሬደዋ ፣አዳማ ፣ ወላይታ እና ሶዶ ባሉ ከተሞች ኔት ወርክ የማሻሻል እና መልሶ ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ እንደሆነም ገልፀዋል።
በቅርቡም በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በኤሌክትሪክ ሃይል በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው የገለጹት፡፡
ችግሩን ለመቀነስም ህብረተሰቡ አደጋ ሊፋጥሩ ይችላሉ ብሎ የተመለከታቸውን የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት በ905 ነጻ የስልክ መስመር እና በአቅራቢያው ባለው የተቋም ቅርንጫፍ ጥቆማ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ መልዕክቶችን ለመቀበል 80 ጥሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ 905 ነጻ የስልክ መስመር መኖሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ ÷ በቀጣይ ነጻ የስልክ መስመሩን ሀገር አቀፍ ለማድረግ እየተስራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.