Fana: At a Speed of Life!

ከኦሮሚያ ክልል ለመከላከያ ድጋፍ ይዞ የተንቀሳቀሰው ልዑክ ጎንደር ላይ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በግንባር ለሚፋለመው ሀይል 650 ሰንጋ በሬዎችን እና 680 በግና ፍየል ድጋፍ ይዞ ጎንደር ከተማ ሲደርስ አቀባበል ተደረገለት።

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ድባቅ ለመምታት በግንባር የሚታገለውን የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ በስንቅና በሞራል ለመደገፍ ከኦሮሚያ ክልል 6 ዞኖች እና 12 የከተማ አስተዳደሮች ናቸው አጋርነታቸውን ለማረጋገጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንደሻው ብርሃን ተናግረዋል።

በሰሜን ሶስት ግንባሮች እየተዋጉ ላሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይል ሚሊሻና ፋኖዎች የኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ጦርነት በድል ለመወጣት ጉልበት እንዲሆን በማሰብ 650 በሬዎች እና 680 በግና ፍየሎች ድጋፍ መደረጉን አስተዳዳሪው አብራርተዋል።

አስተዳዳሪው ምንም እንኳን የሽብር ቡድኑ በአማራ ክልል ጦርነት የከፈተ ቢሆንም አላማው ኢትዮጵያን ማጥፋት ነው ያሉ ሲሆን ይህን አሸባሪ ቡድን በጋራ በመቆም ማፅዳት ይገባል ብለዋል።

አባገዳ ከማል ኢብራሂም በበኩላቸው” ለኢትዮጵያ ህልውና የሚዋደቀውን ሀይል በግንባር ተገኝታችሁ አበረታቱልኝ ብሎ የኦሮሚያ ህዝብ ስለላከን ነው በአካል በመገኝት ስንቅ ለማድረስ የመጣ ነው” ብለዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተደረገላቸው አቀባበል ጥሩ ነበር ያሉት አባገዳ በጎንደር ከተማ ህዝብ የተደረገላቸው አቀባበልም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ከሶስት ቀናት በፊት በግንባር ተገኝተው ሰራዊቱን ያበረታቱት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን አስታውሰዋል።

በአጭር ጊዜ የገቡትን ቃል በተግባር በማረጋገጣቸው እናመሠግናለን ብለዋል ከንቲባው።

በኢትዮጵያ ላይ በሽብር ቡድኑ የተቃጣውን ጥቃት በድል ለመወጣት በጋራ መተባበር የሚጠይቀበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ነው ያሉት አቶ ሞላ መልካሙ።

የጎንደር ከተማ የሀገር ሽማግሌ ተወካዮችም በወንድሞቻችን የተደረገው ድጋፍ አሸባሪውን ቡድን ድባቅ ለመምታት ለሰራዊቱ ተጨማሪ አቅም ይሆናል ብለዋል።

ከኦሮሚያ ክልል ተወክለው ድጋፍ ይዘው የመጡ ልዑካንን የጎንደር ከተማ ህዝብና አመራሮች ተቀብለዋቸዋል።

ምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.