Fana: At a Speed of Life!

ከኮሮና ቫይረስ ራስን ለመጠበቅ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት መነሻውን ቻይና ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን አውጇል።

በኢትዮጵያም የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ራስን ከዚህ ቫይረስ ለመጠበቅም የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይገባል

1. በሕይዎት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

2.ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ

3. የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣

4. እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ፣

እንዲሁም በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ደግሞ÷

ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም፣ ትኩሳትና እንደሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣

በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ ቫይረሱ ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት መሽፈን፣

አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀሙበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

8335

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.