Fana: At a Speed of Life!

ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ የስራ ፍቃድ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወለድ አልባ ባንክ የስራ ፍቃድ ርክክብ በዘምዘም ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ መካከል ተደረገ።

ዘምዘም ባንክ ከ13 አመታት የአክሲዮን ምስረታ በኋላ ወደስራ የሚያስገባውን ፍቃድ ዛሬ አግኝቷል።

ባንኩ በዘርፉ ከፍተኛ የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጁነት አላቸው ያላቸውን ወይዘሮ መሊካ በድሪን ዋና ስራ አስፈጻሚው አድርጎ አስተዋውቋል።

የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውና ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ የስራ ፍቃድ በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ባንኩ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎትን በመላ ሃገሪቱ ለማዳረስና ውስንነት ያለበትን የፋይናንስ ተደራሽነት ተግባራዊ ለማድረግ አጋዥ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዘምዘም ባንክ ተጨማሪ የባንክ አገልግሎት ሰጭ እንደመሆኑ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ሊጠቀምበት የሚችል አማራጭ ባንክ እንደሚሆን እምነታቸውንም ገልጸዋል።

በተስፋዬ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.