Fana: At a Speed of Life!

ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን የማሻሻል ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብአት፣ ሂደትና ውጤት ተለክተው ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ትምህርት ቤቶቹን እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ፕሮግራም ባለሙያ አቶ አሸናፊ ጌታቸው ÷በአገሪቱ የመደበኛ ትምህርት ከሚሰጡ ከ45 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መካከል በ2011 ዓ.ም ከ21 ሺህ በላይ ለሆኑት የደረጃ ምደባ ተሰጥቷል ብለዋል።
የደረጃ ምደባውን ካገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል 90 በመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች መሆናቸው መረጋገጡንም ባለሙያው አስታውቀዋል።
ከደረጃ በታች የሆኑት ትምህርት ቤቶች የዳስ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በግብአት፣ ሂደትና ውጤት በኩል የሚጠበቅባቸውን ያላሟሉ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
ከደረጃ በታች በሆነ ይዘት ትምህርት እየሰጡ ያሉ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በቀጣዮቹ 10 አመታት ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ችግሩን ለመፍታትም በተፋጠነ መንገድ ትምህርት ቤቶችን ወደ ደረጃ ማምጣት ከተያዙ አማራጮች ውስጥ መሆኑንም አመላክተዋል።
የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዲያመጣ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ጥረትን ለመደገፍ ትምህርት ቤቶች ፣ወላጆችና የሚመለከታቸው አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.