Fana: At a Speed of Life!

ከድጋፍ በተጨማሪ ግምባር በመሰለፍ ለሀገራቸው መስዋእትነት እየከፈሉ መሆኑን ወጣቶች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህውሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን ጥፋት ለመግታት በበሬ ወለደ የሀሰት ወሬ ከመደናገር ግምባር ድረስ ሄዶ ዋጋውን መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ የኮምቦልቻ ከተማ ወጣቶች ገልጸዋል፡፡
ወጣቶቹ በመደራጀት ለጸጥታ ሀይሉ ስንቅ ከማቅረብ ባለፈ÷ ግምባር ድረስ በመዝለቅ መስዋእትነት እየከፈልን ነው ብለዋል።
በዛሬው እለትም በግንባር በመገኘት ከ1ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት ለጸጥታ ሀይሉ ስንቅ አቀብለዋል፡፡
ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየትም÷ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱት ግንባር በመግባት ሲዋጉ÷ ቀሪዎቹ ደግሞ ለሠራዊቱ ሎጂስቲክ በማሟላት መስዋእትነት እየከፈልን ነው ብለዋል።
ሀገር ሊያጠፋ የመጣ ሀይልን መዋጋትና መስዋእትነት መክፈል ክብር ነው ያሉት ወጣቶቹ÷ አሸባሪው
እሰከሚቀበር ተጋድሏችን ይቀጥላልመ ነው ያሉት፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.