Fana: At a Speed of Life!

ከጎንደር መተማ ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጎንደር መተማ መስመር ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የ8ኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ዋና አዛዥብርጋዴር ጄነራል ናስር አባዲጋ አስታወቁ፡፡

በሽንፋ በኩል በአራት አቅጣጫ የገባው የህውሓት ወራሪ ኃይልና ግብረአበሮቹ በከፈቱት ጦርነት ምክንያት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱን ዋና አዛዡ ተናግረዋል።
አብዛኛው የጠላት ኃይል በመደምሰሱና የተወሰነ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ተገቢው ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ ተቋርጦ የነበረው ከጎንደር መተማ መስመር ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የ8ኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ዋና አዛዥብርጋዴር ጄነራል ናስር አባዲጋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

መስመሩ በመዘጋቱ ከጎንደር በአብርሃጅራ በኩል ወደ መተማ ዜጎች አማራጭ ትራንስፖርት ለመጠቀም ተገደው መቆየታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.