Fana: At a Speed of Life!

ከጣና ኃይቅ እምቦጭን በማስወገድ ለተሳተፉ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጣና ኃይቅ የተከሰተውን የእሞቦጭ አረም ለማስወገድ በተካሔደው ዘመቻ ለተሳተፉ አካላትና ተቋማት የእውቅና መስጠት ፕሮግራም በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለምባ ቀበሌ ተካሂዷል።

በተደረገው ዘመቻ በሃይቁ ውስጥና ዳርቻ ከተወረረው 4ሺህ 300 ሔክታር ውስጥ 94 በመቶ የሚሆነውን ማስወገድ መቻሉ ተነግሯል።

በዚህ የእምቦጭ ማስወገድ ዘመቻ ስራ 3 መቶ 96ሺህ አርሶ አደሮች የተሳተፉ ሲሆን ለጉልበት ክፍያና ሌሎች ወጪዎች 75 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አስታውሰዋል።

የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.