Fana: At a Speed of Life!

ከጥራጥሬ የተዘጋጀው ምግብ በብዛቱ በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ከጥራጥሬ የተዘጋጀው ምግብ በብዛቱ በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

ምግቡ ምስር፣ ሩዝ፣ ባቄላና ሌሎች የጥራጥሬ እህሎችን አንድ ላይ በማቀላቀል የተዘጋጀ ጣፋጭ የህንድ ምግብ መሆኑ ተገልጿል።

በሂማሻል ፕራዲሽ ግዛት የተዘጋጀውን ምግብ 25 ምግብ አብሳዮች ለአምስት ሰዓታት ያክል በጋራ አብስለውታል።

ይህ ምግብ ኪችዲ የሚባል ሲሆን ምግቡን ለማዘጋጀት 1 ሺህ 994 ኪሎ ግራም ጥራጥሬዎችን ምግብ አብሳዮቹ ተጠቅመዋል።

ምግቡን አዘጋጅተው ለመጨረስም 405 ኪሎ ግራም ሩዝ፣ 190 ኪሎ ግራም ባቄላ፣ 90 ኪሎ ግራም ቅቤ፣ 55 ኪሎ ግራም ቅመም እና 1 ሺህ 97 ሊትር ውሃ ተጠቅመዋል።

ምግቡ ለሂንዱ ፌስቲቫል የተዘጋጀ ሲሆን በፌስቲቫሉ ላይ ለሚታደሙ ጎብኝዎች ይቀርባል ነው የተባለው።

ምግቡ ተዘጋጅቶ ካለቀ በኋላም በመጠኑ ብዛት በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ) ላይ ሰፍሯል።

ከዚህ ቀደም በ 907 ኪሎ ግራም የሚመዝን ምግብ ይህን ክብረ ወሰን ይዞ መቆየቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.