Fana: At a Speed of Life!

ከፅንፈኛው የህወሓት ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አይደረግም- የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የፌዴራል መንግስት እየወሰደ ከሚገኘው ህግን የማስከበር እምርጃ ጋር ተያይዞ ከፅንፈኛው የህወሓት ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት እንደማያደርግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ገለፁ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ እነርሱን ወደ ጠረቤዛ ዙሪያ ሳይሆን ለፍትህ ነው የምናቀርበው ያሉ ሲሆን ከወንጀለኞች ጋር ድርድር አይኖርም ብለዋል።
የአፍሪካ እህት ወንድሞች የህወሓት ቡድን አመራሮች እጃቸውን እንዲሰጡ ጫና ቢፈጥሩ ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ ያሉት አማካሪው ይህን ሀሳብ ግልፅ ለማድረግ ወደ መቐለ መጓዝ አያስፈልግም ብለዋል ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ።
አቶ ማሞ በመጪዎቹ ቀናት የሞዛምቢክ ፣ የላይቤሪያ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ መሪዎች አዲስ አበባ እንደሚገቡ የገለፁ ሲሆን መንግስት እየወሰደ ከሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ወደ መቐለ መጓዝ እንደማይችሉ ጠቁመዋል።
መንግስት የተባበሩት መንግታት ድርጅት ኤጀንሲዎች በትግራይ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ በሚችለው አቅም እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.