Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ምርት ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድ ኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታዉ አቶ እሸቴ አስፋው ለፋና ብሮካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ቀድሞ ይገባ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የነዳጅ ምርት በአሁኑ ሰዓት 3 ሚሊየን ሊትር በቀን ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ይገኛል ብለዋል።

በተጨማሪም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዲፖዎች በቂ ክምችት ያላቸው በመሆኑ በአቅርቦት ላይ ምንም ስጋት እንደሌለ ገልጸዋል።

በመዲናዋ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩት ሰልፎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ እሸቴ ይህ የተፈጠረው አፋር አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምከንያት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ ችግሩ በመቀረፉ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪዎች በብዛት ወደ ሀገር እየገቡ ናቸው ብለዋል።

ይሁን እንጂ አንዳንድ የነዳጅ ማዲያዎችና ተጠቃሚዎች እጥረት እንዲፈጠር የሚያደረግ ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ሚኒስትሩ ባደረገው ቁጥጥር በማረጋገጡ ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

አያይዘውም ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪም ይሁን የአቅርቦት ችግር ባለመኖሩ ሁሉም ተረጋግቶ ስራውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በመሀመድ አሊ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.