Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የደም ግፊትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ የዓለም የደም ግፊት ቀን “ደም ግፊትዎን በትክክል ይለኩ፣ ደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ ፣ ረጅም እድሜ ይኑሩ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የደም ግፊት ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ (ስትሮክ) ፣ የልብ ህመም፣ ለኩላሊት በሽታ ለመሳሰሉ የጤና ችግሮች እና የድንገተኛ ሞት ዋና መንስኤ መሆኑ ይነገራል፡፡

በመሆኑም በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በሚያዘጋጁት ምግቦች ላይ የሚጨምሩትን የጨው መጠን በመቀነስ ፣አትክልትና ፍራፍሬ አዘውትረው በመመገብ፣ ቅባትና ስኳር የበዛባቸውን ምግቦች መመገብ በመቀነስ፣ ሲጋራ አለማጨስና ለሲጋራ ጭስ ተጋላጭ ባለመሆን ጤናን መጠበቅ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በተጨማሪም ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠን መውሰድ በማቆም፣ የደም ግፊት መጠናችንን አዘውትሮ በመለካትና በመከታተል እንዲሁም በጤና ባለሙያ የታዘዘን መድሀኒት በአግባቡ በመውሰድ ጤናን መጠበቅ ይገባል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.