Fana: At a Speed of Life!

ከ 101 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጳጉሜ 5 እስከ መስከረም 6 ድረስ ከ101 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ናቸው ተብሏል፡፡

በዚህም የገቢ ኮንትሮባንድ 99 ሚሊየን 494ሺህ 237 ብር ሲሆን÷ ወጪ ደግሞ 2 ሚሊየን 345ሺህ 048ብር በድምሩ የ101ሚሊየን 839ሺህ 285ብር ግምት አላቸው መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ከኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ተመላክቷል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ዕቃዎች ውስጥ በድምሩ 80ሚሊየን 322 ሺህ 616 ብር የሚሆነው በአዲስ አበባ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በገቢ እና በወጪ የተያዘ ነው ተብሏል፡፡

ከነዚህ ውስጥ የዋጋ ግምታቸው 50 ሚሊየን 260 ሺህ 216 ብር የሆኑት ኤሌክትሮኒክሶች እንዲሁም የዋጋ ግምታቸው 27 ሚሊየን 606ሺህ 384ብር የሆኑት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ናቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.