Fana: At a Speed of Life!

ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 28 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት አሥራ አንድ ቀናት ከ 46 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከሐምሌ 16 እስከ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መሆኑ ተገልጿል።
 
ከተያዙት ዕቃዎች መካከል ስማርት ስልኮች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት፣የብር ጌጣጌጥ፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ ልባሽ ጨርቆች ይገኙበታል ተብሏል።
 
ከዚህ በተጨማሪም ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ተሽከርካሪዎች እና ከሀገር ሊወጣ የነበረ ቡና መያዙን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.