Fana: At a Speed of Life!

ከ11 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ 150 አዳዲስ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ግዥ ተፈጸመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ11 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ 150 አዳዲስ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ግዥ መፈፀሙን  ኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

የገቢና ወጪ ጭነቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማጓጓዝ እና የድርጅቱን የሎጅስቲክስ አቅም ለመገንባት የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ግዥ እንደተፈፀመ ተነግሯሎ፡፡

ተሽከርካሪዎቹ ከቻይናው የከባድ ተሸከርካሪዎች አምራች ከሆነው ሲኖትራክ ኢንተርናሽናል እንደተገዙ እና እያንዳንዳቸው ከ400 ኩንታል በላይ የመጫን አቅም እንዳላቸው የድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ አቶ ወንድሙ ደንቡ ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከቻይና ቲያነጂ ወደብ ፊንፊኔ በተባለችው መርከብ የተጫኑት ተሸከርካሪዎቹ  በተያዘው የፈረንጆቹ ወር 2021 መጨረሻ አካባቢ ጅቡቲ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተሸከርካሪዎችን በ2012 በጀት ዓመት የመግዛት ሂደት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በበጀት ዓመቱ የቴክኒካል መመዘኛውን አሟልተው የተገኙ ተጫራቾች ባለመገኘታቸው ድጋሚ ጨረታ ወጥቶ ግዥው በተያዘው 2013 በጀት ዓመት በታቀደለት የጊዜ ገደብ ተፈፃሚ እንደሆነ ከድርጅቱ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ተሽከርካሪዎቹ በ11 ሚሊየን 430 ሺህ ዶላር ወጪ የተገዙ ሲሆን ይህ የገንዘብ መጠን ተሽከርካሪዎቹን ከተመረቱበት ቦታ እስከ መጫኛ ወደብ ማድረስን ያካተተ ነው፡፡

በኢባትሎአድ በኩል ተሸከርካሪዎችን ከምርት ሂደታቸው ጀምሮ ክትትል የሚያርግ የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ክትትል ሲያርግ የቆየ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹ ጅቡቲ በሚደርሱበት ወቅት የቴክኒክ ኮሚቴው በቦታው ተገኝቶ ርክክብ የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የተሽከርካሪዎች መገዛት ማዳበሪያ እና መሰል ብትን ጭነቶችን በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ ለማጓጓዝ እንደሚረዳ እና በዘርፉ ያለውን የተሸከርካሪ እጥረት በመጠኑ እንደሚቀንስም አቶ ወንድሙ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳ

የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.