Fana: At a Speed of Life!

ከ110 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ110 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሀምሌ 29 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ቅርንጫፎች ባደረገው ክትትል ነው የገቢ እና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችን የያዘው።

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሀዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ እና አዋሽ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ናቸው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል መባሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ዘጠኝ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.