Fana: At a Speed of Life!

ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምስት ቀናት ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት)፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል።

እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ከፍተኛ ቁጥጥር ብዛት ያላቸው የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን ÷በዚህም 120 ሺህ  ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.