Fana: At a Speed of Life!

ከ20 ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ ክለብ አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢትዮጵያ 20ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር  አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መስጠቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

ከታህሳስ 14 እስከ 16 የቆየው ስልጠና የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ እና ልማት ዳይሬክቶሬት መስጠቱ ታውቋል፡፡

በሀገር ውስጥ ኢንስትራክተሮች የተሰጠው ስልጠና በንደፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ነበር ተብሏል፡፡

በ2012 ከሚካሄደው የኢትዮጵያ ወጣቶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በፊት ለአሰልጣኞች ማነቃቂያ ለመስጠትና በቀጣይ ለሚታሰበው  ከ20 ኣመት በታች የአፍሪካ ውድድር በየክለቡ የሚገኙ ወጣቶችን ብቁና ዝግጁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ 17 ክለቦች መሳተፋቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.