Fana: At a Speed of Life!

ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 13፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፈው አንድ ሳምንት  ግምታዊ ዋጋቸው ከ23 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር  መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከግንቦት 05 እስከ 11ቀን 2012 ዓ.ም የተያዙት የኮንሮባንድ ዕቃዎች በህገ-ወጥ መንገድና በቱሪስት ስም የገቡ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህም  ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ፣ አዳዲስ እና አሮጌ አልባሳት፣ ኤለክትሮኒክስ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሀኒቶች፣ ምግብና የምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ ሞባይሎች፣ ጫት፣ ሲጋራ እንዲሁም የዜጎቹን አእምሮ የሚጎዳ አደገኛ እፅና ሺሻ  በተለያዩ የሀገሪቱ  የጉምሩክ ኬላና መቆጣጠሪያ ጣቢዎች መያዛቸውን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በሌላም በኩል ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ብዛቱ 14 ሺህ 474 የቱርክ ሸጉጥ ጥይት እና 3 ስታር ሽጉጥ ከመተማ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ሳለ ሰርባ ኬላ ፍተሻ ላይ ከፌደራል ፖሊስ አባላትና ከክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ ከ2 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

ከዚያም ባለፈ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በቦሌ አየር መንገድ እና ሞጆ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በኩል የሚገቡ ዕቃዎችን ሠነድና ንግድ በማጭበርበር ለማስተላለፍ የተሞከረ ቢሆንም በተደረገው ጥብቅ ፍተሻ ከ 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ተጨማሪ ታክስና ግብር እንዲከፈል  መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.