Fana: At a Speed of Life!

ከ32 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ አሸባሪው ህወሃት ጉዳት ማድረሱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ32 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ አሸባሪው ህወሃት ጉዳት ማድረሱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ።

በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በወደሙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

መግለጫውን እየሰጡ የሚገኙት የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ፥ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ እያንዳንዳቸው ከ50 እስከ 800 የሚደርሱ ሰራተኞችን ቀጥረው ሲያሰሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

በምግብና ምግብ ነክ፣ ብረታ ብረት፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር እና በጨርቃ ጨርቅ ዘርፎች ላይ የተሰማሩም እንደነበሩ በመግለጫው ተመልክቷል።

በቀጣይ የጉዳት መጠኑን ለይቶ አምራች ኢንዱስትሪዎቹን ወደ ስራ ለማስገባት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ አቶ ሺሰማ ተናግረዋል።

በፈቲያ አብደላ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.