Fana: At a Speed of Life!

ከ5 ቢሊየን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በዚህ ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው 6 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 5 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን በአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን አስታወቀ።
በኮሚሽኑ የደን ልማት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ቢተው ሽባባው እንዳሉት በዚህ ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው ስድስት ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 5 ነጥብ 8 ቢሊየን ችግኝ ተዘጋጅቷል።
በዚህም በመላ አገሪቱ በሚገኙ 126 ሺህ 461 ችግኝ ጣቢያዎች የችግኝ ማፋላት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።
ከዚህም ውስጥ ከ3 ቢሊየን በላይ የደን ችግኝና ከ 2 ነጥብ 7 ቢሊየን በላይ የጥምር ደን ግብርና ችግኝ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
ለችግኝ ተከላው የሚሆን 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት የተለየ መሆኑን ጠቁመው ዝግጅቱም በመንግስትና በህብረተሰቡ አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ለስራው ስኬታማነት ለግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎች እየተሰጠ እንደሚገኝና እነሱም ለአርሶ አደሮችና የችግኝ ተከላ ለሚያካሂዱ አካላት ስልጠና እንደሚሰጡ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.