Fana: At a Speed of Life!

ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደብሊው ኤ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የደብሊው ኤ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ።

በደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው ፋብሪካ በቀን 1 ሚሊየን 350 ሺህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም አለው።

ፋብሪካው አሁን ላይ ለ1 ሺህ 500 ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ሲጀምር የምርት የሰራተኞቹ ቁጥር በሶስት ፈረቃ እስከ 6 ሺህ ይደርሳል ተብሏል።

ከፋብሪካው አጠቃላይ ምርት 40 በመቶው የሰሊጥ ዘይት ይሆናል ነው የተባለው።

የሃገር ውስጥ ፍላጎትን መሰረት በማድረግም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሀገር ውስጥ የዘይት ፍጆታን 60 በመቶ ለመሸፈን እንደሚሰራ ተገልጿል።

የምርት መቆራረጥ እንዳይፈጠርም ፋብሪካው ምርቱን ወደ ገበያው በቅርቡ በተደራጀ መልኩ ያስገባል ነው በመግለጫው የተባለው።

ፋብሪካው በዓመትም እስከ 18 ቢሊየን ብር የስራ ማስኬጃ ወጪ ይኖረዋል።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.