Fana: At a Speed of Life!

ከ50 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳታፊ የሆኑበት ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በማስመልከት ከ50 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳታፊ የሆኑበት ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስቀል አደባባይ ተካሄደ፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሴቶች ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡

በወቅቱ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተገኙ ሲሆን ሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፣የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰትን ለመከላከል በጋራ መደራጀት እና መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሴቶች ዛሬ መብታቸውን ያውቃሉ ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ለዚህም መላው ሴቶች በአብሮነት፣ በአንድነት፣ በፍቅር፣ በመቻቻል፣ በመተሳሰብ የተደራጀ እና የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ሴቶችን በቀላሉ በማታለል እና በማጭበርበር ድጋፋቸውን እናገኛለን ብለው የሚያስቡ አካላት ካሉ ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው ያሉት ወይዘሮ አዳነች ሴቶች ዛሬ መብታቸውን ያውቃሉ ብለዋል፡፡

ለሴቶች የእናውቅላችኋላን ጊዜ አልፋል፤ ሁሉም ሴቶች ስለ መብታቸው ያውቃሉ ብለዋል፡፡

እንዲሁም ከሰሞኑም በተለየ ሁኔታ ለሴቶች ገንዘብ ይታደላል ብለው የራሳቸውን አጀንዳ ከማራመድ ባለፈ እናቶችን በማንገላታት ለሴቶች ያላቸውን የተሳሳተ አስተሳሰብ እያሳዩን በመሆኑ ሴቶች ሊጠነቀቁ እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡

በመስቀል አደባባይ በተካሄደው እና ከ50 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳታፊ በሆኑበት ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣተቱ   ሴቶች ፣ አንጋፋ ሴት አትሌቶች እና አርቲስቶች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.