Fana: At a Speed of Life!

ከ50 አመታት በላይ የዘለቀው የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ዉጤቶችን ማስመዝገቡን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፥ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ዉጤቶችን ማስመዝገቡን አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ዣዖ ዢዋን ከኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ጋር በፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት ተወያይተዋል ።

በውይይታቸውም ወቅት የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በሀገሪቱ እየተደረጉ ያሉ የፖለቲካና ማህበራዊ ሪፎርሞች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት ላይም እየተሠሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ጅምሮች እያስመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል ።

ከ50 አመታት በላይ የዘለቀው ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፥ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ዉጤቶችን ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

እንዲሁም የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሳተፍ ለስራ ዕድል ፈጣራ ያደረጉት አስተዋጽኦ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል አፈጉባኤዉ።

አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት የኮቨድ -19 ወረርሽኝ ለመከላከል ባደረገው ጥረት ዉስጥ የቻይና መንግስትና ህዘብ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ያዳረጉት ድጋፍ በታሪክ የሚወሳ መሆኑን ገልፀዋል ።

በተጨማሪም በሁሉም ክልሎች ለቻይና ኢንቨስተሮች አስፈላጊ ትብብር አንዲደረግና የአፍሪካ -ቻይና ግንኙነት እንዲጠናከር የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚሰራ አፈጉባኤ ለአምባሳደሩ ገልጸዋል ።

አዲሱ የቻይና አምባሰደር ዣዖ ዢዋን በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሁሉንአቀፍ ሪፎም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው አሁንም የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚያደርገውን ሁለተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ለአፈጉባኤው ገልጸዋል ።

በተለይም ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የመሠረተ ልማት ስራዎች ለማገዝ የቻይና መንግስት ቁርጠኛ አቋም ያለው መሆኑን አምባሳደሩ አሳዉቀዋል ።

ኢትዮጵያም የአፍሪካ -ቻይና ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጀ ለመሸጋገር ለምታደርገው ጥረት የቻይና መንግስት ትልቅ አክብሮት የሚሰጥ መሆኑን አምባሳደሩ ተነግረዋል ።

በመጨረሻም ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር የላትን ግንኙነት አጠናክራ የምትቀጥል ይሆናል ማለታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.