Fana: At a Speed of Life!

ከ59 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው አንድ ሳምንት ከ59 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ ገቢ እና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ ክትትል በማድረግ መያዙን የገቢዎች ሚስቴር አስታወቀ፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ውስጥ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ቡና፣ የውጭ ሀገራት ገንዘብ፣ የጦር መሣሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መዋቢያ ቁሳቁሶች፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች እና የተለያዩ አልባሳት ይገኙበታል፡፡

እቃዎቹን ከመያዝ ባሻገር የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን በማዘዋወር ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ለተገኘው ውጤት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞችነ እንዲሁም የፀጥታ እና አጋር አካላትን አመስግነው ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.