Fana: At a Speed of Life!

ከ6 ሺህ በላይ የክላሽንኮቭ ጥይት በግመል ሲያጓጉዙ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ 6 ሺህ 74 የክላሽንኮቭ ጥይት በግመል ሲያጓጉዙ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የወረባቦ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሰይድ አብዱ እንደገለጹት ግለሰቦቹ ትናንት ጥይቱን በግመል ጭነው ሲያጓጉዙ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ግለሰቦቹን ለህግ ለማቅረብም ምርመራ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.