Fana: At a Speed of Life!

ከ600 ሺህ በላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሃብታቸውን አስመዝግበዋል-ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከ600 ሺህ በላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሃብትና ንብረታቸው ማስመዝገባቸውን አስታወቀ።

የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ እንዳሉት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሃብት ምዝገባ ተከናውኗል።

በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በልማት ድርጅቶች፣ በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተሻለ መልኩ ሃብት አስመዝግበዋል ብለዋል።

በዚህም ኮሚሽኑ በዕቅድ ከያዘው 95 በመቶውን ማሳካት እንደቻለ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር ቅሬታን ለመፍታት ከዕቅድ ዝግጅት እስከ ትግበራ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውና በ52 ከተሞች የድጋፍና ክትትል ሥራ መሰራቱ ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.