Fana: At a Speed of Life!

ከ8 ሺህ በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ምዝገባው ለ10 ቀናትም ተራዝሟል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ምዝገባው ለ10 ቀናትም መራዘሙንም የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ምዝገባውም ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

የምዝገባ ጊዜው ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም መጠናናቁን ገልጿል፡፡

ሆኖም ከተጠቃሚው ወደ ቢሮው በሚመጡ ጥያቄዎች በመነሳት ምዝገባው ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለመመዝገብ እየፈለጉ በሲስተም መጨናነቅ ምክንያት ላልተመዘገቡ፤ ከመረጃው መዳረስ አንጻር ተጠቃሚው በቂ ግንዛቤ ባለመያዙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ያልሰሙ የአማራጭ ቤት ልማት ፕሮግራሙን ፈላጊዎች በመኖራቸው ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘሙን ቢሮው ገልጿል፡፡

በመሆኑም መመዝገብ እየፈለጉ በተለያየ ምክንያት ቀኑ ያለፋቸው ተጠቃሚዎች የምዝገባ ጊዜው  ከሚያዚያ 6 እስከ ሚያዚያ 15/ 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ  መምጣት  ሳያስፈልጋቸው  በቀጥታ /Online/  በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et  አማካኝነት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በምዝገባ ወቅት ችግር የገጠማቸውን የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ ከሚያዚያ 18-20/2013ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በቢሮው ቀርበው ቅሬታችውን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በማህበር ቤት ፕሮግራሙ መካተት አቅሙ እና ፍላጎቱ ለሌላችው ደግሞ ነባሩ የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ግንባታ ስራ በተለመደው አሰራር የሚቀጥል መሆኑን ቢሮው አመልክቷል ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.