Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ በጸጥታ ችግር እንዲቆይ የሚፈልጉ ስላሉ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሆን አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ውስጥ እንዲቆይ የሚሠሩ አካላት በመኖራቸው ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሆን አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገላጹ።
የቡልድግሉ ወረዳ መሠረታዊ የሚሊሻ ስልጠና ያጠናቀቁ ሠልጣኞችን ዛሬ አስመርቋል።
በመርሃ ግብሩ ርዕሠ መስተዳድሩ እንደገለጹት÷ የሕወሓት ተላላኪዎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እያደረሱት ባለው ጥቃት በዜጎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በጸጥታ ችግር ውስጥ የቆዩትን መተከልና ካማሺ ዞኖችን ጨምሮ ክልሉን ከጸረ-ሠላም ኃይሎች ነጻ ለማድረግ የፌዴራልና የክልሎች የጸጥታ አካላት በጋራ የተቀናጀ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
የጸጥታ ሥራውን ለማጠናከር በየወረዳዎቹ የሚሊሻ አባላትን የማሠልጠንና የማስታጠቅ ሥራ መከናወኑንም ጠቁመዋል።
ዘላቂ ሠላም የሚገነባው በጸጥታ አካላት ብቻ ባለመሆኑ÷ ህብረተሰቡ አሁንም በክልሉ ሠላም እንዳይኖር የሚሠሩ አካላት መኖራቸውን ተገንዝቦ ከጸጥታ አካላት ጎን ሆኖ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅም ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.