Fana: At a Speed of Life!

ክልል አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)”የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማስፋፋት በአካሉ የዳበረ ፣ በአዕምሮው የበለፀገ ፣ ጤንነቱ የተጠበቀ ብቁና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንተጋለን” በሚል መሪ ቃል በወላይታ ሶዶ የማስ ስፖርት የማህበረሰብ አቀፍ እንቅሰቃሴ ተካሂዷል።

የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የማህበረስብ አቀፍ እንቅስቃሴ አረጋውያንን ረጅም ዕድሜ በጤና ለማኖር፣ ጤናማ እናቶች እንዲኖሩና ፣በአካልና በአዕምሮ የዳበሩ ህፃናትና ወጣቶች እንዲሁም በተለያዩ የስራ ቦታዎች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡ ስራተኞች እንዲኖሩ ያግዛል።

አቶ ሳሙኤል የማህበረስብ ተሳትፎ ስፖርት ጤናን በመጠበቅ ምርታማነትን ሲጨምር ፣አብሮ የመኖርና የመራዳዳት ባህልን በማዳበር የሀገሩን ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ዜጋ እንዲኖር የጎላ ድርሻ አለው ብለዋል።

በማህበረሰብ ተሳትፎ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሽዋስ አለሙ በዚህ ወቅት እንዳሉት ስፖርት የተለያዩ በሽታዎችን ከመከላከል በተጨማሪ ዕድሜን ፣ጾታንንና ማንነትን ሳይለይ በጋራ የሚሰራ በመሆኑ አስታራቂና ችግር ፈቺ ነው።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በየትኛውም ቦታ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ የሽዋስ ስፖርት ምርታማና የወንድማማችነት ስነ-ልቦና በማምጣት ሰላምና ብልፅግና እንዲኖር የሚያደርግ ሲሆን ዝግጅቱ እንዲሳካ ያደረጉትን ለክልልና ዞን ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ።

በዝግጅቱ ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎችና የተለያዩ ጤና ቡድንና ስፖርት ክበብ አባላት ተሳታፊ ሲሆኑ፤ የተሳትፎ ስፖርቱ በቀጣይም ዘወትር ቅዳሜ በከተማው እንደሚደረግ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.