Fana: At a Speed of Life!

ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጭ አስጊ ደረጃ ላይ አለመድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጭ አስጊ አለመሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ድርጅቱ የጃፓኗን መርከብ ሳይጨምር ከቻይና ውጭ ባሉ ሃገራት የቫይረሱ አሳሳቢነት አስደንጋጭ የሚባል አለመሆኑን ገልጿል።

በጃፓኗ ዲያመንድ ፕሪንስስ መርከብ 44 በቫይረሱ አዲስ የተጠቁ ሰወች የተገኙ ሲሆን፥ በመርከቧ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 218 መድረሳቸው ተነግሯል።

ከቻይና ውጭም በ24 ሃገራት ሁለት ሞት ሲመዘገብ 447 ሰወች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

በቫይረሱ በቻይና አዲስ 121 ሞት ሲመዘገብ አጠቃላይ የሟቾቹ ቁጥርም 1 ሺህ 380 ደርሷል ነው የተባለው።

እስከ ትናንት ድረስም የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 55 ሺህ 748 መድረሱን የቻይና ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን አስታውቋል።

በሁቤይ ግዛትም ትናንት 116 ሰዎች ሲሞቱ 4 ሺህ 823 ሰወች በቫይረሱ ተይዘዋል ተብሏል፤ ይህም ከቀደመው ቀን አንጻር ቀንሶ ታይቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.