Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከልና ቁጥጥርን ለመደገፍ፣ የጤና መረጃ ስርአቱንና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚያስችል ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉ ሴቭ ዘ ችልድረን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የተደረገ ሲሆን 505 ታብሌቶች ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የመረጃ አያያዝና ልውውጥን ማዘመን እና የኮሙዩኒኬሽን ስርዓትን መዘርጋት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የጤናውን ዘርፍ የሚያሳድጉ ውሳኔዎችን ለመስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው ሴቭ ዘ ችልድረን ላደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው ድጋፍ ያመለክታል።

የሴቭ ዘ ችልድረን ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኪን ኦግቶጊላሪ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.