Fana: At a Speed of Life!

ወርልድ ቪዥን በሰሜን ጎንደር ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች 80 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የምዕራብ አማራ የአደጋ ምላሽ ፕሮግራም በሰሜን ጎንደር ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች 80 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዞኑ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና  ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሠላም ይሁን ሙላት÷ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የምዕራብ አማራ አደጋ ምላሽ ፕሮግራም በዞኑ ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የዕለት ደራሽ ምግብን ጨምሮ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎችን፣ አልባሳት እና ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ፕሮግራሙ በዛሪማ ለሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በየቀኑ 7 ሺህ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች ውሃ እያቀረበ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ መሰል  ሰብዓዊ ድጋፎች ፋይዳቸው የላቀ  መሆኑን አውስተዋል።

በመጠለያ ጣቢያዎቹ ያለው ችግር ዘርፈ ብዙ ነው ያሉት አቶ ሠላም ይሁን÷ያለውን ችግር በመቅረፍ ረገድ ሁሉን አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የምዕራብ አማራ የአዳጋ ምላሽ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ከተማ በበኩላቸው÷ የሰው ልጆችን ችግር መጋራትና የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ የፕሮግራሙ ዋነኛ አላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮግራሙ ሌሎች አጋሮችን በማስተባበር ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በቀጣይ ሶስት ወራትም በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ህጻናትና ታዳጊዎች ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ለማድረግ በትኩረት  እንደሚሰራ ገልጸው÷የሰብዓዊነት ተግባሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እስከሚመለሡ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በላይነህ ዘለዓለም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.