Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ወይዘሮ አዳነች “የድል አርማ የሃገር ደጀን የህዝብ ልጅ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በተቀዳጀው ድል የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ በከፍተኛ ኩራት ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በሞራል ፣ በገንዘብ፣ በህክምና ሙያ እና በሁሉም መስኮች ከፍተኛ ደጀን ሆነው መቆየታቸውንም አስታውሰዋል።

ይህ ድል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድል ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ አዲስ አበባ የዚህ አይነት አንፀባራቂ ህብረት እና ድል መገለጫ መዲና መሆኗንም ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግንነት ፣ ምሳሌነት እና ቁርጠኝነት ለሀገሪቱ መፃዒ ጊዜ ታላቁን መሰረት እንደተከለ ላረጋግጥ እወዳለሁም ነው ያሉት።

“ደስታውን እና ድሉን ስናጣጥም አብሮነታችንን ከሚበክሉ እኩይ ተግባራት ሁላችንም እየተቆጠብን አንድነታችን እና ክብራችንን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ብቻ በማተኮር የታላቅ ሀገር ባለቤትነታችንን በቀጣይ ድሎችም እናረጋግጣለን” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.