Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ወይዘሮ ሕርቲ ምህረተአብ እና የክልሉ መንግስት አማካሪ የነበሩት ወልደጊዮርጊስ ደስታ፣ እንዲሁም በእነ አባይ ወልዱ የክስ መዝገብ ላይ ከሚገኙ ተከሳሾች ውስጥ አምደማርያም ተፈራ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ በሰርቪስ ማረፊያ እንዲቆዩ ተወስኗል፡፡

በእነ አባይ ወልዱ መዝገብ 9 ሰዎች ቀዳሚ ምርመራ ቀርቦባቸዋል፤ ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ ማረሚያ ይቆዩ ብሎ ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወይዘሮ ሙሉ ገብረእዝግአብሔር በወንጀል ስለሚፈለጉ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.