Fana: At a Speed of Life!

ወደ ትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳታ እንዳይገባ የህወሃት ርዝራዦች እንቅፋት እየሆኑ ነው – መንግስት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ አርሶ አደሮች ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን እንዲያካሂዱና ሰብዓዊ ዕርዳታን እንዲመቻች ቢያደርግም የህወሃት ርዝራዦች ለእርዳታ አሰጣጥ እንቅፋት እየሆኑ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ ፡፡

ከተኩስ አቁም ስምምነቱ እና የመከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ እና ሌሎች ከተሞች ለቆ ከመውጣቱ በፊት የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ አስተባበሪ ኮሚቴ ባለፉት ወራቶች በሶስት ዙሮች ድጋፍ ሲያደርግ ነበረ፡፡

ኮሚቴው በክምችት ደረጃ 4መቶሺህ ኩንታል ስንዴ፣ 2ነጥብ 5 ሚሊየን የምግብ ዘይት እንዲሁም 14ሚሊየን ሊትር ነዳጅ ለህብረተሰቡ ፍጆታ የሚውል እንዲቀመጥ አድርጎ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችም ለተቸገሩ ወገኖች ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግስት ፈቃድ መስጠቱም ነው የተገለጸው፡፡

መንግስት ብሄራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ሳይጥል ለትግራይ ክልል ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ አቅርቦቶች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲደርስ ለመደገፍ በቁርጠኝነት ጸንቶ ይገኛል ፡፡

አሁንም ቢሆን መንግስት የብሄራዊ ደህንነቱን አደጋ ላይ ሳይወድቅ መሰረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ እርዳታዎች ለትግራይ ህዝብ እንዲደርስ ቁርጠኛ አቋም አለው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም መንግስት ማንኛውም እርዳታ ለማድረግ የሚደረጉ በረራዎች መነሻቸውን አዲስ አበባ አድርገው እንዲንቀሳቀሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን ገልጿል፡፡

ይህም የተደረገው የሃገሪቷን ብሄራዊ ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ስላለበት መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም ባለፈው ሳምንት ሁለት በረራዎች በአለም አቀፉ የምግብ ድርጅት አማካኝነት ተካሂደዋል፡፡

መንግስት የሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይዘገዩ በአፋር በኩል የእርዳታ እህል የጫኑ ከባድ መኪናዎች ያለምንም ችግር እንዲገቡ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ይገኛል፡፡

ሆኖም የህወሃት ጁንታ ጥቃት እየፈጸመ የሚገኝ ሲሆን፥ እንደ አብነትም ሃምሌ 11 በሰመራ አባላት መንገድ የእርዳታ እህል በጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት የፈጸመ ሲሆን፥ ይህንንም መንግስት አውግዟል፡፡

ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ለተረጂዎች እርዳታ እንዳይደርስ ማድረጉ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊወገዝ ይገባል ብሏል መንግስት በመግለጫው፡፡

የህወሃት ቡድን ህጻናት ወታደሮችን ለጦርነት በማሰለፍ በኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ላይ እያደረገ ያለውን ትንኮሳ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዘው ይገባልም ነው ያለው፡፡

ሆኖም መንግስት ከልማት አጋሮቹ ጋር በመሆን ለተረጂዎች ምግብ እና መድሃኒት እንዲደርስ ያለመታከት እየሰራ እንሚገኝ ገልጿል፡፡

ወደፊትም ከሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ጋር እርዳታው እንዳይቋረጥና የተጎዱ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ እንደሚሰራ መግለጹን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.