Fana: At a Speed of Life!

ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከታክስ በፊት አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከታክስ በፊት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
ባንኩ ሃያ ሰባተኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል።
በበጀት አመቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ በፈጠረው መቀዛቀዝ ምክንያት በብድር አከፋፈል እና አሰባሰብ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን ተከትሎ የብድር ወለድ ምጣኔ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።
ሆኖም ከ2018 እና 2019 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ47 በመቶ ወይም 342 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ሞላ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት የሰበሰበው የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ከ2018 እና 2019 ከነበረው 23 ነጥብ 5 ቢሊየን ጋር ሲነጻጸር 28 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ወደ 30 ነጥብ 1 ቢሊየን ማደጉን ምክትል ሰብሳቢው አስታውቀዋል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ካፒታልም ወደ 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ያደገ ሲሆን÷ የባንኩ አጠቃላይ ሃብት 38 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መድረሱም ተገልጿል፡፡
ባንኩ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ያሉት ቅርንጫፎችም በበጀት አመቱ መጨረሻ 383 መድረሱን በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.