Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ ቁሳቁሶች በኤሌክትሪክ ሃይል የምትንቀሳቀስ ባጃጅ ሰርቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት የአካባቢ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በኤሌክትሪክ ሃይል የምትንቀሳቀስ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ሰርቷል።

ሙሃመድ ሁሴን የተባለው ይህ ወጣት ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ የዋሉ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ክላሽ የተሰኘ የጦር መሳሪያ መስራቱም ተገልጿል።

የጦር መሳሪያው አንድን ነገር ለመስራት ካሰቡ ቀላል እንደሆነ አሳውቆኛል የሚለው ወጣቱ፥ በዚህ በመነሳሳት በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ መስራት መቻሉን ተናግሯል።

ወጣቱ ባጃጇን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 20 ሺህ ብር የሚጠጋ ወጪ ማውጣቱን ከጃዊ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በቀጣይም በፀሃይ ሃይል እና በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚደረግ ባትሪን በመጠቀም ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ባጃጅ ለመስራት ማቀዱን ጠቁሟል።

ማንኛውም ሰው ያሰበውን ዕቅድ ለማሳካት ተስፋ ሳይቆርጥ የተለያዩ ተሞክሮዎችን መቅሰም እና በተደጋጋሚ መሞከር አስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.