Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሂሩት ከዓለም አእምሮዊ ንብረት ድርጅት ምክትል ዳሬክተር ጀኔራል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ በዓለም አእምሮዊ ንብረት ድርጅት ምክትል ዳሬክተር ጀኔራል ዋንግ ቢንይንግ የተመራ የልኡካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አእምሮዊ ንብረት ድርጅት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት የምትሰራ መሆኑን ወይዘሮ ሂሩት ተናግረዋል።

የዓለም አእምሮዊ ንብረት ድርጅት በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮችን የቴክኖሎጅ እና አዕምሯዊ ንብረት ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ዋንግ ቢንይንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑን በመግለጽ፥በዚህም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ በፍጥነት እያደገች ያለች  ሀገር መሆኗ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ጠንካራ፣ ሁለንተናዊ  እና  አለማቀፋዊ ትብብር  ይበልጥ ለማሳደግ በቅንጅት እንደሚሰራ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.