Fana: At a Speed of Life!

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የገበያ ቁጥጥርን ማጠናከርና የግብይት ሰንሰለት ስርዓትን ማስተካከል ይገባል- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የገበያ ቁጥጥርን በማጠናከር እና የግብይት ሰንሰለቱን ስርዓት በማስተካከል ከአምራች ወደ ሸማች በቀጥታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ በጦር ኃይሎች አካባቢ አዲስ የተገነባውን አሙዲ ፕላዛ ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም ላይ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት÷ የነዋሪውን የገበያ ፍላጎት ለሟሟላት የምርት አቅርቦት መጨመርና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረቡ በከተማዋ የሚታየውን ለኑሮ ውድነት ለመቀነስ ያግዛል ብለዋል።

በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የግብይት ሰንሰለቱን በማሣጠር ከአምራች ወደ ሸማች በቀጥታ ለማቅረብ የሚተጉ ድርጅቶችን የሚያደርጉትን ጥረት የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ገልፀዋል።

አሙዲ ፕላዛ ኩዊንስ ሱፐር ማርኬትን ጨምሮ ሌሎች መሰል ሱፐር ማርኬቶች ለነዋሪው የዕለት ተዕለት ህይወት አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ እንዲያቀርቡ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አክለው ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ላይም ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው እስከ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ሲገበያዩ መመልከታቸውም ተገልጿል።

ሸማቾቹም የሱፐር ማርኬቱ በአካባቢያቸው መከፈት የተለያዩ ምርቶችን በፈለጉበት ሠዓት በአንድ ቦታና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ እንደረዳቸው መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.