Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስአበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አምባሳደር ሙሀመድ ሳሌም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለሀብቶች እያጋጠሟቸው ባሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

በውይይቱ ወቅት ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ ባለሀብቶች በአቅም ግንባታ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በማህበራዊና መሰል የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ቢያተኩሩ የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች ጥቅም ይበልጥ ለማሳደግ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎረሙን ተከትሎ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ ለውጭ ባለሃብቶች ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ሚኒስትር ዲኤታዋ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሙሀመድ ሳሌም በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የተጀመረው የኢንቨስትመንት ማሻሻያ አሁን ካለው በተሻለ ቀልጣፋና ለውጭ ባለሃብቶች ምቹ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

አመቺ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠርም በሁለቱ ሃገራት የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅርርብ መስራት እንዳለባቸው ሁለቱ ወገኖች በነበራቸው ውይይት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.