Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ቤዝ ደንፎርድና ከባንኩ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ባንኩ የአፍሪካ ሴቶችና ወጣቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚሰራቸውን ስራዎች አቅርቧል፡፡
ወይዘሮ ፊልሰን በበኩላቸው የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የትኩረት አቅጣጫዎች አስረድተዋል፡፡
በመጨሻም ሚንስቴር መስሪያ ቤቱና ባንኩ ወደፊትም በተጠናከረ መልኩ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.