Fana: At a Speed of Life!

ዊሊያን በሶስት አመታት ውል አርሰናልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው የመስመር አማካር ዊሊያን የሰሜን ለንደኑን የእግር ኳስ ክለብ አርሰናልን ተቀላቀለ፡፡

ዊሊያን የምዕራብ ለንደኑን እግር ኳስ ክለብ ቼልሲን በመልቀቅ ወደ አርሰናል በነጻ ዝውውር አምርቷል፡፡

የ32 አመቱ ዊሊያን በአርሰናል ለሶስት አመታት ለመቆየት መስማማቱም ነው የተነገረው፡፡

ዊሊያን በፈረንጆቹ 2013 ከሩሲያው አንዚ ማካቻካላ በ30 ሚሊየን ፓውንድ መፈረሙ ይታወሳል፡፡

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ለክለቡ በ339 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

በቼልሲ የነበረው ስምምነት ማብቃቱን ተከትሎ ክለቡ “በምፈልገው” መልኩ ኮንትራቴን እንዳድስ አልፈለገም በሚል ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡

በሰሜን ለንደኑ ክለብ በሰማያዊዎቹ ቤት ያገኘው ከነበረው ሳምንታዊ ክፍያ የተሻለ ያገኛል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.